በመጪው መስከረም ወር የሚከበሩትን የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን ህዝባችን ያለ ምንም ስጋትና እንግልት በደስታና በሰላም ያከብር ዘንድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ከውሃና ኤሌክትሪክ አቅርቦት እስከ ጽዳትና አደጋ መከላከል የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

አድማጮቻችን! በበዓላቱ ወቅት የሚያስፈልጉዎትን ዋና ዋና መረጃዎችና የነጻ ጥሪ መስመሮች እንደሚከተለው አዘጋጅተንላችኋል፦”

·       የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፦ የተሰበሩ መስመሮች ጥገና የተደረገላቸው ሲሆን፤ ማንኛውም የውሃና ፍሳሽ ችግር ሲያጋጥማችሁ በ 906 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ትችላላችሁ።

·       የኤሌክትሪክ ኃይል፦ የመስመር ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የካርድ መሙያና አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች በበዓል ዋዜማና ዕለት ቀኑን ሙሉ ክፍት ይሆናሉ። ለማንኛውም ጥያቄ በ 905 ይደውሉ።

·       እሳትና ድንገተኛ አደጋ፦ በበዓሉ ወቅት አደጋዎችን ለመከላከል ዝግጅት የተደረገ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና ችግር ሲፈጠር በ 939 ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

·       ጽዳትና የመብራት መሰረተ ልማት፦ የከተማዋን ጽዳት ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት የተደረገ በመሆኑ አድማጮቻችን ቆሻሻን በአግባቡ በመያዝ፣ እንዲሁም የ24 ሰዓት የጎዳና ላይ መብራት መሰረተ ልማቶችን በመንከባከብ ከተማችንን እንድናስ ውብ እንድናደርግ ጥሪ ቀርቧል።

በድጋሚ “በዓላቱ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆኑልዎ እንመኛለን!”

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

የኢትዮጲያዊያን

ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *