በሪያድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሳውዲ አረቢያ ለሚኖሩ አሜሪካውያን ዜጎች አስቸኳይ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ

ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካውያን ከየመን ጋር በሚያዋስኑ የሳውዲ አረቢያ የድንበር አካባቢዎች ከማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡና ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የጥንቃቄ ማስጠንቀቂያው የተሰጠው ከየመን ድንበር በኩል የሚሰነዘሩ ድንገተኛ ጥቃቶችና የፀጥታ ስጋቶች በመጨመራቸው ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።

በተጨማሪም በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ የአሜሪካ መንግሥት ሰራተኞች ከየመን ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኙ ቀጠናዎች እንዳይጓዙ እገዳ ተጥሏል ዘገባው የroya news English ነው።

ልዑል ወልዴ

መስከረም 6/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *