በኢትዮጵያ ሰነደ ሙአለነዋዮች ገበያ የዜጎችና የባለሀብቶች ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

የገበያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ዮዲት ካሳ እንደገለጹት፤ ገበያው ሥራ ከጀመረ ወዲህ ከባንክ ቁጠባ ባሻገር ለዜጎች ተጨማሪ የቁጠባና የኢንቨስትመንት አማራጭ እየሆነ ይገኛል።

አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችም በዘመናዊ የሞባይል ቴክኖሎጂ ታግዘው በቀላሉ በገበያው መሳተፍ የሚችሉበትን አሰራር ተደራሽ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዋና አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በገበያው በስፋት እየተሳተፉ ያሉት የፋይናንስ፣ የቴሌኮምና የሪል እስቴት ኩባንያዎች ናቸው።

ይሁን እንጂ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ እንዲሁም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ካፒታላቸውን ማሳደግ እንዲችሉ የአማራጭ የገበያ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት በሰነደ ሙአለነዋዮች ገበያው በሳምንት ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ግብይት እየተካሄደ ነው።

ወደፊት እንደ ኢንሹራንስና የጡረታ ፈንድ ያሉ ግዙፍ ተቋማዊ ባለሀብቶች ገበያውን ሲቀላቀሉ፤ የግብይት መጠኑ ይበልጥ እንደሚያድግና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተመላክቷል።

ልዑል ወልዴ

መስከረም 7/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *