የየመን ሀይሎች ሁቲዎችን ኢሊማ ማድረጋቸውና አሜሪካ በቀጥታ የመሳተፍ ዕድልን ውድቅ ማድረጓ ተገለፀ
በሳውዲ በሚመራው ጥምረት እና በሁቲዎች መካከል ያለው ውጊያ እየተጠናከረ ሲመጣ፣ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ላለው የየመን መንግሥት ያላትን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጣለች።
በሌላ በኩል፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኦማን ከሁቲ ተወካዮች ጋር በቀጥታ መወያየታቸውን የሮይተርስ ምንጮች ገልጸዋል።
በስብሰባው ላይ ሁቲዎች በአሜሪካ መርከቦች ላይ ጥቃት የመሰንዘር ፍላጎት እንደሌላቸውና ለ2025ቱ የተኩስ አቁም ስምምነት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የየመን የመንግሥት ኃይሎች በጥምረቱ እገዛ በሞቻ ዙሪያ በሚገኙ የሁቲ ይዞታዎች ላይ ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን፣ በማሪብ ደግሞ የድሮን ጥቃቶችን ፈጽመዋል።
ሁቲዎች በበኩላቸው በማሪብ ላይ የሳውዲ ኤፍ-15 ተዋጊ ጀት መትተው መጣላቸውን ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሳውዲ አረቢያ የሚሳይል መጥለፊያ ክምችት እያለቀባት በመሆኑ እንደ ፈረንሳይ፣ ፓኪስታን፣ ግብፅ እና ዩናይትድ ኪንግደም ካሉ አጋሮቿ የአየር መከላከያ ድጋፍ ጠይቃለች።
የሳውዲ ዋና መሣሪያ አቅራቢ የሆነችው አሜሪካም ቢሆን፣ ከኢራን ጋር በተያያዘው ውጥረት ምክንያት የራሷ የመጥለፊያ ሚሳይል ክምችት እየቀነሰባት መሆኑ ተገልጿል።
የአሜሪካ መካከለኛው ዕዝ ከሳውዲ ጋር ያለውን የረጅም ጊዜ ወታደራዊ ግንኙነት በመጥቀስ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧሎ።
ሳራ ዮሐንስ
መስከረም 7/2019 ዓ.ም
