52 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ ስርአት ዉስጥ ባለመግባታቸዉ ከዘርፉ እንዲወጡ ቢነገራቸዉም፤ ተቋማቱ ከዘርፉ አለመዉጣታቸዉ ተነገረ

ግንቦት 2016 መጨረሻ ላይ ለዳግም ምዝገባ  ከተቋማቱ ሰነዶችን መቀበል መጀመሩን የሚገልፀዉ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን፤ የዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ጥሪ ከተደረገላቸዉ 102 ተቋማት 84ቱ የምዝገባ ጥሪዉን ባለመቀበላቸዉ ከዘርፉ እንዲወጡ መናገሩን ገልፆል።

ከነዚህ ዉስጥ በህጋዊ መንገድ የሚጠበቅባቸዉን አሟልተዉ  የመዉጫ ፍቃድ ወስደዉ ዘርፉን ዘግተዉ የወጡት 32ቱ ብቻ እንደሆኑ ከኢትዩ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የባለስልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጀምበሩ አለማየሁ ተናግረዋል።

ተቋማቱ የያዟቸዉን ተማሪዎችን ወደ ሌላ የዳግም ምዝገባ መስፈርቱን ወደ አሟላ ተቋም ማዘዋወር ባለመቻል እና የግብር ጉዳዩች ጋር በተያያዘ 52ቱ ተቋማት ከዘርፉ ለመዉጣት ህጋዊ የመዉጫ ፍቃድ እንዳልተሰጣቸው አቶ ጀምበሩ ለኢትዩ ኤፌም ተናግረዋል ።

ባለስልጣኑ ተቋማቱ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተሰማርተው ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እና የህግ እርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል።

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በበኩላቸው የወጣው ይህ መመሪያ አማራጭ በማጣት ከገበያዉ እንዲወጡ ያደርጋል የሚል ቅሬታን እያነሱ ቀጥለዋል።

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ኘሬዝደንት ዶ/ር ሞላ ፀጋዬ  የዳግም ምዝገባዉ ሂደት በድጋሜ ለዉይይት መቅረብ እንዳለበት ገልፀዋል።

በሀገሪቱ ስርአተ ትምህርት አዉድ ላይ አሁንም መረጋገጥ ያልቻለዉን ጥራት ለመምጣት የተቋማትም ሆነ ተማሪዎችን የመመዘኛዎች ልክ’ነት የራሱን ቅሬታ የሚያስተናግድ ሆኖ እየተሰማ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 11/2019

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *