የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት(CFA) አስራ አንድ ሀገሮችን ያስተሳሰረውን የናይል ተፋሰስ በፍትሃዊነት ለመምራት መፅደቁ ይታወሳል።
ስምምነቱ ወደ ተግባር ተሸጋግሯል መባሉን ተከትሎ የሚቋቋመው አስፈፃሚው የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን ግን እስካሁን ወደ ስራ መግባት አልቻለም።
ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት በዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማሪካ ዶ/ር ዘበነ ላቀዉ፤ የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ የኮምሽንነት የሽግግር ጊዜ ላይ መገኘቱን ገልፀዋል።
ኢንሼቲቩ በፈረንጆች 1999 ስምምነት እስኪደረስ ድረስ የተቋቋመ የመሸጋገሪያ ተቋም ነበር ያሉት ዶ/ር ዘበነ፤ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መፅደቁን ተከትሎ ኮሚሽን መቋቋሙን ገልፀዋል።
ኮሚሽኑን ወደ ስራ ለማስገባት ቀሪ የሽግግር ስራዎች መኖራቸዉን የገለፁት አማካሪዉ፤ በሌላ በኩል ግን ኮሚሽኑ ወደ ስራ ላለመግባቱ ግብፅ ተፅዕኖ አላት ብለዋል።
ዶ/ር ዘበነ እንደሚሉት፤ግብፅ አንዳንድ የተፋሰሱ ሀገራትን በመያዝ የምታደርገው እንቅስቃሴ ኮሚሽኑ ስራ ላለመጀመሩ ትልቅ ቦታ አለዉ ብለዋል።
የናይል ተፋሰስ ኮሚሽንን ወደ ስራ ለማስገባት የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ፈራሚ ሀገራት አጥብቀዉ መስራት አለባቸዉ ሲሉ ዶ/ር ዘበነ ገልፀዋል።
ግብፅ እስካሁን ስምምነቱን ተቀብለው ካለፀደቁት ሀገራት ዉስጥ ትገኝበታለች።
ቁምነገር አየለ
መስከረም 18/2019 ዓ.ም
