የአሜሪካና ቻይና የ30 ቢሊየን ዶላር የታሪፍ ቅነሳ ስምምነት ዝርዝር ይፋ ተደረገ

አሜሪካ ቀደም ሲል ከቻይና ጋር የተደረሰውን እና ከሁለቱም ሀገራት 30 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የገቢ ምርቶችን የሚሸፍን የታሪፍ ማሻሻያ ስምምነት ዝርዝር ይፋ አደረገች።

በዚህ ስምምነት መሠረት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ምርቶች አብላጫ ፈቃድ የተሰጣት ሀገር የታሪፍ ምጣኔ ተጠቃሚ ትሆናለች።

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ ይህ ስምምነት ከመስከረም 20 እስከ 23 በኒውዮርክ እና ዋሽንግተን በሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚና ንግድ ልዑካን መካከል ከተካሄዱት ውይይቶች ከተገኙ ውጤቶች መካከል ነው።

ሁለቱም ሀገራት በየሀገሮቻቸው ሕግ መሠረት አስፈላጊ የሆኑ ሂደቶችን ካጠናቀቁ በኋላ የታሪፍ ቅነሳውን በጋራና በሰዓቱ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ጄሚሰን ግሪር እንደተናገሩት፤ ‹‹የትራምፕ አስተዳደር በግብርና እና የኃይል ምርቶች ግዥ የተገቡ ቃሎች መከበራቸውን በማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ ባልሆኑ ምርቶች ላይ ሚዛናዊ ንግድን በመከተል እንዲሁም ለአሜሪካ ገበሬዎች፣ አምራቾች እና ሰራተኞች የገበያ ዕድል በማመቻቸት ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ የንግድ ግንኙነትን ያጠናክራል።››

በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በንግድ ምክክር ማዕቀፋቸው ስር የሁለትዮሽ ንግድ ምክር ቤት ለመመስረት የተስማሙ ሲሆን፤ዋና ዓላማውም የሁለትዮሽ ንግድን ማሳለጥ ነው።

በአሜሪካ የከሰል ድንጋይ ወጪ ንግድ ላይ የተጣለው ታሪፍ በዚህ የ30 ቢሊየን ዶላር የጋራ ቅነሳ ማዕቀፍ ውስጥ የተካተተ ሲሆን፤ይህም በ2027 እና 2028 ቻይና ከአሜሪካ የምታስገባውን የከሰል ድንጋይ መጠን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተገልጿል።

ሁለቱ ሀገራት የኢንቨስትመንት ምክር ቤት እና በቻይና ንግድ ሚኒስቴርና በአሜሪካ የንግድ ተወካይ ቢሮ በጋራ የሚመራ የግብርና የሥራ ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል።

የግብርና የሥራ ቡድኑ የመጀመሪያ ስብሰባውን ከ2026 ማጠናቀቂያ በፊት ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ሀና ሰይፉ

መስከረም 18/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *