በኢትዮጵያ ያለፉት አምስት ዓመታት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ17 ሚሊዮን ወደ 65 ሚሊዮን እንዲሁም የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ከ51 ሚሊዮን በላይ ማደጉ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ የ50 ዓመት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉዞ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የ5 ዓመታት የዲጂታል ስኬቶች (ስትራይድ 2.0) በሳይንስ ሙዚየም መከበር በጀመሩበት ወቅት ነው።
 
በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር በለጠ ሞላ እንደተናገሩት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በዲጂታል ዘርፉ የተመዘገበው እቅስቃሴ ከሌሎች አሥርት ዓመታት በላይ የሚመዝን ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ ነው። አክለውም የሳይንስና ምርምር ውጤቶች ከቤተ-ሙከራ ወደ ፋብሪካና ማሳ በመሸጋገር የሕዝብን ሕይወት በተግባር መለወጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
 
በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው፣ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ማነቆዎች መፈታታቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይ አርቲፊሻል ኢንቴለጀንስን በመጠቀም የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥና ብቁ የሰው ኃይል ማፈራት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
 
 
መስከረም 19/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *