በ6ኛው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት መጀመሪያ ላይ የAI ቴክኖሎጂ የተቀናጀባቸው አዳዲስ መተግበሪያዎች ይፋ ተደረጉ

“ዲጂታል ፈጠራ ለአካታች ቱሪዝም” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው 6ኛው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት መድረክ ላይ የቱሪዝም ዘርፉን በዲጂታል ፈጠራና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በማዘመን ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል::

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማስተዋወቅን ጨምሮ፣ የጉዞ እቅዶችን ማዘጋጀት፣ የንግድ እንቅስቃሴዎችን እና የጎብኚዎችን ልምድ ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል ብለዋል።

ሚኒስትሯ የሀገሪቱ የቱሪዝም ፖሊሲ በዲጂታል ቴክኖሎጂና በAI እንዲደገፍ አቅጣጫ መያዙን ገልጸው፣ የዲጂታል ሽግግሩ ጥቂት አካባቢዎች ላይ ብቻ ሳይወሰን ፍትሃዊ፣ አካታችና ሰዎችን ማዕከል ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በዝግጅቱ ላይ የAI ቴክኖሎጂ የተቀናጀበት የኦሮሚያ ቱሪዝም ድረ-ገጽን ጨምሮ ሌሎች የዲጂታል መድረኮች ይፋ ሆነዋል።

እነዚህ የዲጂታል መድረኮች የክልሉን ተፈጥሮአዊና ባህላዊ ሀብቶች በዲጂታል መንገድ ለዓለም በማስተዋወቅ ጎብኚዎች በቀላሉ እንዲጎበኙ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ በበኩላቸው፣ የቱሪዝም ሳምንቱ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት የመጡ የዘርፉን ተዋናዮች የሚያገናኝ ትልቅ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘንድሮው መርሃ ግብርም ከ22 ሀገራት የተወጣጡ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ዝግጅቱ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል።

ለ3 ቀናት በሚቆየው በዚህ የቱሪዝም ሳምንት በዲጂታል ቱሪዝም፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በአካታች ቱሪዝምዙሪያ ያተኮሩ የፓናል ውይይቶችና ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ይካሔዳሉ።

ሀና ሰይፉ
መስከረም 19/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *