የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለውን ጥቃት ኮንነዋል

የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ በጋዛ እየተካሄደ ያለውን አስከፊ ጦርነት አጥብቀው አውግዘዋል።

በባህረ ሰላጤው አካባቢ ለሚታየው ውድመት ተጠያቂ የሆኑት አካላት ሁሉ “የጦር ወንጀለኛ” ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ“ፒርስ ሞርጋን አንሴንሰርድ” ፕሮግራም ላይ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፥የሃማስ የጥቅምት 7 ጥቃት መኮነን ያለበት “ጭፍጨፋ” ቢሆንም፣ የእስራኤል ምላሽ ግን ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና ሆስፒታሎችንና ትምህርት ቤቶችን ኢላማ ያደረገ ነው ብለዋል።

እስራኤል በጥቅምት 2025 የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት በየቀኑ በመጣስ ከ1ሺህ 4መቶ በላይ ፍልስጤማውያንን መግደሏንና የጋዛን 70 በመቶ መሬት መቆጣጠሯን በመጥቀስ ፥ዶሃ የጀመረችው የሰላም ጥረት በእስራኤል እጅ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ መስተጓጎሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም እስራኤል የሃማስ ከፍተኛ አመራሮች ለድርድር ተሰብስበው በነበሩበት ወቅት በኳታር መዲና ዶሃ ላይ የሰነዘረችውን የሚሳኤል ጥቃት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የጣሰና በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ “አስታራቂን ማጥቃት” ሲሉ አውግዘውታል።

በአሁኑ ወቅት ኳታር ከፓኪስታን ጋር በመሆን በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ እያሸማገለች እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በክልሉ ያለውን ጦርነት ለማቆም መሰረታዊ የሚባሉ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ሳራ ዮሐንስ

መስከረም 20/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *