የቢሮው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኩሳ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፤ ባንኩን የማቋቋም ጥናቱ በአምራቾች ዘንድ የሚታየውን የብድርና የካፒታል እጥረት ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት ያለመ ነው።
ኃላፊው አክለውም ጥናቱ ተጠናቆ ወደ ተግባር ሲገባ ዘርፉን በልዩ ሁኔታ የሚደግፍና የረጅም ጊዜ ብድር የሚያቀርብ ተቋም እንደሚኖር ገልጸዋል። ይህ የፋይናንስ አቅርቦት ማደጉ አምራቾች የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ሁሉም የንግድ ባንኮች ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ቅድሚያ ሰጥተው ብድር እንዲያቀርቡ በተቀመጠው የመንግስት አቅጣጫ መሰረት ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም አቶ ጳውሎስ ጠቁመዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም
