በሀገሪቱ ያጋጠመውን የኮንዶም እጥረት ለመቅረፍ ለ18 ወራት የሚሆን በቂ አቅርቦት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ

ዲኬቲ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ያጋጠመውን የስነ-ተዋልዶ ጤና ግብአቶች እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል ለ18 ወራት የሚሆን በቂ የኮንዶም አቅርቦት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን እና በ2026 ለማሰራጨት ካቀደው እስከ 40 ሚሊዮን የሚደርስ መጠን ውስጥ ከ85 በመቶ በላይ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል።

የአለም አቀፍ የእርዳታ አቅርቦቶች በመቀነሳቸው ያጋጠመውን እጥረት ለመፍታት ተቋሙ በግዥ፣ በሎጅስቲክስ እና በስርዓት ዝርጋታ ሰፊ የሪፎርም ስራ መስራቱን የኦፕሬሽን ክፍል ሀላፊ አቶ አሳይየ ደምሴ የገለጹ ሲሆን፣ በተጨማሪም የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና የአለም ጤና ድርጅት መስፈርቶችን ያሟላ ዘመናዊ ማዕከላዊ መጋዘን ገንብቶ ስራ ላይ ማዋሉን አብራርተዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን  እና የአለም ጤና ድርጅት  ደረጃዎችን ያሟላ ዘመናዊ ማዕከላዊ መጋዘን በመገንባትና በማስመረቅ የመድኃኒቶችና የኮንዶም ጥራት ሳይበላሽ እንዲጠበቅ ተደርጓል።

አቅርቦቱንም በሶሻል ማርኬቲንግ አሰራር ድጎማ በማድረግ ለግል ጤና ተቋማት፣ ለፋርማሲዎች፣ ለኪዮስኮች፣ ለቡፌዎችና ለሆቴሎች በተመጣጣኝ ዋጋ የማዳረስ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

አቅርቦቱ በድጎማ ለግል ጤና ተቋማት፣ ለፋርማሲዎች፣ ለኪዮስኮችና ለሆቴሎች በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሰራጨ እንደሚገኝና በ7 የክልል ማዕከላት በኩል ጥያቄ በቀረበ በ24 ሰዓት ውስጥ አቅርቦት የሚያደርስ ፈጣን አሰራር እንዲሁም የደንበኞች የአጭር ስልክ ጥሪ ማዕከል መዘርጋቱንም አክለው ገልጸዋል።

ለዓለም አሰፋ

መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *