እስራኤል በጋዛ በየቀኑ ለ4 ሰዓታት ውጊያ ለማቆም መስማማቷን አሜሪካ አስታወቀች
እስራኤል ከስምምነቱ የደረሰችው ሰዎች ከጦርነት ቀጠና እንዲወጡ እና ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረስ መንገድ ለመከፍት እንደሆነም ተነግሯል።
የአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት ዋይተ ሃውስ እስራኤል የወደሰችውን እርምጃ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲል አድንቋል።
የአሜሪካ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪብሪ፤ የመጀመሪያው የሰባዓዊ የውጊያ ማቆም ተግባር ከትናት ጀምሮ እንደሚተገበር አስታውቀዋል።
“የውጊያ ማቆም በሚተወጅበት ሰዓት በሰሜን ጋዛ እና አካባቢው ምንም አይነት ወተደራዊ እንቀስቃሴ እንደማይኖር ተነግሮናል” ብለዋል ቃል አቀባዩ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዳልደረሰች ገልጻ፣ ነገር ግን ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረግ ለአጭር ጊዜ ውጊያዎችን ልታቆም እንደመትችል ተናግራለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም
