በአበረገለ ጭላ ወረዳ ከ95 ሺህ በላይ ሰዎች አፈጣኝ የምግብ እርዳታይፈልጋሉ ሲል የአበርገለ ጭላ ወረዳ አስታወቀ፡፡

በትግራይ ክልል በምትገኘው አበርገለ ጭላ ወረዳ አንድ መቶ ዘጠኝ ሺህ ነዋሪዎች የሚኖሩ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 95 ሺህ 160 የሚሆኑ ሰዎች አፋጣኝ የምግብ ረድኤት የሚፈልጉ ናቸው ተብሏል፡፡

የአርገለጭላ ወረዳ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሀበን አሰፋ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ በወረዳው ከፍተኛ የሆነ የምግብ እርዳታ የሚፈልግ ህዝብ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በወረዳው 13 ቀበሌዎች ያሉ ሲሆን በስድስት ቀበሌዎች የሚኖሩ 42 ሺህ ገደማ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ ይገኛሉ፡፡

አበርገለ ጭላ ወረዳ ከፍተኛ በርሃማ አካባቢ ሲሆን  ያለፉትን አምስት ዓመታት ደግሞ በከፍተኛ ድርቅ በመመታቱ ዜጎች አርሰው መኖር አቅቷቸዋል፡፡

ከሰሞኑ ከተለያዩ ባለሀብቶች እንዲሁም ከረድኤት ድርጅቶች የተወሰነ እርዳታ እንዳገኙ የሚናገሩት አቶ ሀበን ከመንግስት በኩልም በቂ ባይሆንም ድጋፎች መኖራቸውን ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በድረቁ ዙሪያ ጣብያችን ያነጋገራቸው ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች የመብት ተሟጋቾች ድርጅትም በትግራይ ክልልም ሆነ በአማራ ክልል ያለው የድርቅ ሁኔታ አሳሳቢ ወደ ሆነ ደረጃ ደርሷል ይላሉ፡፡

በሀገሪቱ የተከሰተው ድርቅ በተመለከተ የዓለም አቀፍ ረጂ ደርጅቶች ርብርብ ይጠይቃል የሚሉት የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መብሪህ ብርሃነ መንግስት ለነዚህ ድርጅቶች ጥሪ ሊያደረግ ይገባል ሲሉ አመላክተዋል፡፡

ከሰሞኑ በፌደራል መንግስትና በትግራይ ግዚያዊ አስተዳዳር እየተደረገ የሚገኘው እሰጣአገባ ለህዝቡ የሚጠቅም ባለመሆኑ ከዚህ ዓይነት ሁኔታ መውጣት አለባቸው ሲሉ ይናገራሉ፡፡

ከዚህ በላይ የዜጎች ህይወትን ለማዳን በቁርጠኝነት ጥረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ የአበርገለ ጭላ ወረዳ በድርቁ ምክንያት በተከሰተ ርሃብ 91 ሰዎች መሞታቸውን መግልፁ ይታወሳል፡፡

ጥር 06 ቀን 2016 አ.ም
በአቤል ደጀኔ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *