የአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር አብዛኞች ስብሰባዎችና ኮንፈረንሶች ከከተማዋ ውጭ መካሄዳቸው ሆቴሎች ስራቸው እንዲቀዘቅዝ አድርጓል አለ፡፡

የአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ፕሬዚደንት ወይዘሮ አስቴር ሰሎሞን አብዛኛው ስብሰባም ሆነ ኮንፍረንስ የሚካሄደው ከከተማዋ ዉጭ ባሉ ሆቴሎች መሆኑ በከተማዋ ውስጥ ያሉ ሆቴሎች ገበያቸው ኢንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዉስጥ አሁን ላይ የሆቴል ስራ አስደሳች አይደለም ነዉ ያሉት ፡፡
በተጨማሪም በሃገሪቱ ባለዉ የሰላምና ፀጥታ ችግር እንዲሁም በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ወቅት የሆቴል ዘርፉ ተጎድቶ ነበረ ያሉት ወይዘሮ አስቴር ፤ ባለሆቴሎች ከባንኮች የተበደሩትን ገንዘብ መመለስ የሚችሉበት አቅም ላይ እንዳልሆኑ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

በመጨረሻም ወ/ሮ አስቴር ገበያዉ እንዲነቃቃ ለማድረግ የተለያ ተግባራት እየተተገበሩ እንደሚገኝ ነግረዉናል፡፡

በልዑል ወልዴ

ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *