ለሳምንታት በሕዝብ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ኬንያ ፕሬዝደንት የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን በተኑ።

ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ በዛሬው ዕለት የወሰዱት እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው።

ፕሬዝደንት ሩቶ የካቢኔያቸው ተቀዳሚ ዋና ጸሐፊ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝደንት ራጋቲ ጋቻጉ ሲቀሩ ሌሎቹን ሚኒስትሮቻቸውን በሙሉ ማሰናበታቸውን መናገራቸውን ከናይሮቢ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ፕሬዝደንቱ እርምጃውን የወሰዱት የሕዝባቸውን ድምፅ በመስማት መሆኑን ተናግረዋል።

ከሥልጣን ይልቀቁ የሚለው የሕዝብ ጥያቄና ግፊት ነው ሲል ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል።

ሐምሌ 4 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *