የስልጠና ማዕከሉ እየተገነባ ያለው በሃዋሳ ሲሆን ግንባታው ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭን ይጠይቃል፡፡
በሱስ የተጠቁ ወጣቶች ማገገሚያ የሚሆን ሆስፒታል ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ በወላይታ ሶዶ እየተገነባ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
የኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን እንዳስታወቀችው
በሱስ ለተጠቁ ማገገሚያ እና የስልጠና ማዕከል ለሚገነባው ተቋም ፤ ዓላማውን በሚደግፉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን በሚደረግ ድጋፍ ሲሆን፤ ግንባታዎች ከ2 እስከ 3 ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስትያን ህብረት ፕሬዚደንት ፖስተር ፃዲቁ አብዶ ፣ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዛሬው እለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝተዋል።
የዘንድሮ መልካም ወጣት “መልካም ወጣት ወደ ብርታት ” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ተነግሯል።
የዘንድሮው መልካም ወጣት ሀምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚጀምር ሰሆን፤ ለ6 ቀናት ቆይታን በማድረግ ጷግሜ 2 ስልጠናው የሚጠናቀቅ ይሆናል ተብሏል።
በዘንድሮ መልካም ወጣት ከ30 ሽህ በላይ ወጣቶች ይሰለጥናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፤
በእሌኒ ግዛቸው
ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም
