በፍልስጤም የሚኖሩ ሙስሊም እና ክርስቲያኖች ሰላም የሚያገኙበት ጊዜ ሳይርቅ በፍጥነት የሰብዓዊ ድጋፍ እና ትብብር ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ከፖፕ ፍራንሲስ ጋር በስልክ መነጋገራቸዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ከፖፕ ፍራንሲስ ጋር ባደረጉት የስልክ ንግግር ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን እስራኤል የሃማሱን መሪ ኢስማኤል ሃኒዬህ መግደሏ እና በሊባኖስ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ አገሪቱ ለክልሉ፣ ለዓለም እና ለሰብዓዊነት ስጋት መሆኗን ያሳያል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ እስራኤልን ከሚደግፉ አገራት ጋር ፖፕ ፍራንሲስ እንዲነጋገሩ እና ከዚህ በላይ ለቀጣናዉም ሆነ ለዓለም ፖለቲካ፣ ደህንነት እና ማህበራዊ ትስስር ስጋት የሆነ ቋሚ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ሊያስቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡
እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለችዉ ጥቃት ከፍ ብሎ አሁን ላይ ዘር ማጥፋት ደረጃ ላይ ደርሷል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በስፍራዉ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ቀዉስ መኖሩንም አክለዋል፡፡
እስራኤል አንዳንድ አገራት በሰጧት የዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚክ እና ወታደራዊ ጥላ ስር ሆና ነዉ ጥቃቱን እያደረሰች ያለችዉ ብለዋል፡፡
ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
