የኢሕአፓ ዋና ጸሃፊ ደስታ ጥላሁን  ከፓርቲው መልቀቃቸውን ተናገሩ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ  በዋና ጸሃፊ ደስታ ጥላሁን ከፓርቲው መልቀቃቸውን ለጣቢያችን  በላኩላት ይፋዊ ደብዳቤ አረጋግጠዋል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት ከ አባልነት አንስቶ እስከ ሥራ አስፈፃሚ ድረስ   በተለያዩ የሃላፊነት ስፍራዎች ማገልገላቸውን ያስታወሱት ስራ  አስፈጻሚዋ   በይፋ መልቀቃቸውን ገልፀዋል።

ለመልቀቃቻ ምክንያት በእነዚህ ዓመታት ድርጅቱን ሊያዘምኑና ዘመኑን የሚመጥን ቁመና እንዲኖረው ለማስቻል የተለያዩ ሃሳቦችን ብሰነዝርም  አባላቱ  ከቁምነገር ውስደው ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው ነው  ብለዋል።

በዚህም ድርጅቱን መልቀቃቸውን  ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ለፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ግልባጭ ባደረጉትና ፊርማቸው ባረፈበት ደብዳቤ አሳውቀዋል።

በለአለም አሰፋ

ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *