በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 101 የትራፊክ አደጋዎች በደንገጎ መንገድ ላይ መከሰቱ ተነገረ

እስከ ሀምሌ 30 ድረስ በደረሱ አደጋዎች የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

በደንገጎ መንገድ ላይ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች 9 ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የተናገሩት  በድሬደዋ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የግንዛቤ ማስጨበት እና ማሳደግ ማስተባበሪያ ሃላፊ ኢንስፔክተር ጌትነት ዳባ ናቸው፡፡

እንዲሁም ከደረሱ 101 የትራፊክ አደጋዎች መካከል ቀሬዎቹ ቀላል  የአካል ጉዳት ሲሆን፤ በንብረት ላይ ጉዳቶች መድረሳቸው ተመላክቷል፡፡

ተሸከርካሪዎች በዕለቱ ወደ ድሬደዋ ከተማ እደሚገቡ እና በተመሳሳይ የሚወጡበት ሁኔታ በመኖሩ 24 ሰዓት የትራፊክ ፍሰት በደንገጎ መንገድ ላይ እንደሚኖር ተገልጿል፡፡

የደንገጎ መንገድ ጠመዝማዛ እንዲሁም ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት በመኖሩ የትራፊክ አደጋ እዳይከሰት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም አሁን ያለንበት የክረምት ወቅቱ መሆኑን ተከትሎ በተቻለ መጠን አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ነሐሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *