በጣና ሃይቅ የእንቦጭ  አረም በሌላ አቅጣጫ መከሰቱ ተነገረ

የዘንድሮ ክረምት ጠንከር ያለ በመሆኑ አረሙ እንደሚስፋፋ ግምቶች መኖራውን የጣና ሀይቅ እና  ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃ ማልማት ኤጀንሲ የመጤ እና ተስፋፊ ዝርያ  ክትትል እና ቁጥጥር  ተወካይ ዳይሬክተር አቶ መዝገቡ ዳኛው ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል፡፡

በጣና ሀይቅ ላይ አረሙ በሰሜን እና በሰሜን ምስራቅ የሀይቁ ክፍል የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በደቡብ ምዕራብ  መከሰቱን ገልፀዋል፡፡

ይህም ከዚህ አልፎ በምዕራብ በኩል የሚገኘውን የሀይቁን ክፍል ሊሺፍን ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በዚህ አከባቢ ደግሞ አረሙ ከገባ የማይወጣበት ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል፡፡

በሚቀጥለው በጀት አመት ከዚህ በፊት ሲሞከሩ ከነበሩ አማራጮች ሌላ ፤ በተመረጡ ሳይቶች ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በምርምር ደረጃ ሲሰራ የቆየ ወይብሎችን በማራባት እንቦጩን እንዲመገቡ እና አረሙ እንዳይስፋፋ የማድረግ ስራዎችን ተግባራዊ እናደርግናን ብለዋል፡፡

ለውጥ ማምጣቱን ለመለየትም  ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ከ 2 እስከ 3 አመት ሊወስድ እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

የእንቦጭ አረም አሁንም ትኩረት እንደተነፈገው የሚናገሩት አቶ መዝገቡ አረሙ ከዚህ በበለጠ እየተስፋፋ ስለሚሄድ የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛ እርብርብ ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ሐመረ ፍሬው

ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *