በሆስፒታሉ የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሃላፊ ዶ/ር ሞላልኝ ውብአንተ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእሳት ቃጠሎ ህክምና የሚታወቀው ሆስፒታሉ ባሳለፍነው የ 2016 በጀት ዓመት 16 ሺ 6መቶ 38 ታካሚዎችን በድንገተኛ ክፍል ተቀብሎ የህክምና አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 2 መቶ 10 የሚሆኑት ከቃጠሎ ጋር በተገናኘ የህክምና አገልግሎት ያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በድንገተኛ ክፍል የህክምና አገልግሎት ካገኙት መካከል 3 መቶ 83 ታካሚዎች ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል 9 ሺ 6 መቶ 70 የሚሆኑት ደግሞ ወደ አስተኝቶ ህክምና እንዲገቡ ተደርገዋል ተብሏል።
ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ አካባቢዎች በሪፈር ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጠው ሆስፒታሉ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በአንዳንድ ወራቶች የድንገተኛ ህክምና ክፍሉ ላይ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የመጡ ታካሚዎች ቁጥር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።
ለምግብ ማብሰያነት አገልግሎት ላይ በሚውሉ ጋዞች ፍንዳታ ምክንያት በሚከሰቱ ቃጠሎዎች ሴቶች እና ህጻናት ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ሆነው መለየታቸውን ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል ።
ለአለም አሰፋ
ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም
