በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ በ 45 ቀን ውስጥ 15 ሺ ዮኒት ደም ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ 13 ሺ 2 መቶ 19 ዮኒት ደም መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አስታውቋል ።
ይህም ከእቅዱ 88 በመቶ ማሳካት መቻሉን ያሳያል ተብሏል ።
ከአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች መካከል አራዳ ክፍለ ከተማ 2ሺ 3መቶ 30ዮኒት ደም ሲሰበስብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደግሞ 2ሺ 3 መቶ 93 ዮኒት ደም መሰብሰብ መቻላቸውን ሰምተናል።
እንዲሁም ቦሌ ክፍለ ከተማ ላይ 1440 ዮኒት ደም በ45 ቀን ውስጥ መሰብሰቡ ተገልጿል።
ከሰኔ ጀምሮ እስከ መስከረም 40 ሺ ዮኒት ደም ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በይፋ ግን የደም ማሰባሰቡ የተጀመረው ከሐምሌ 1 ጀምሮ እንደሆነ ተገልጿል ።
የተቆራረጠ ግብአት ባለበት ይህን ውጤት ማምጣት መቻል የሚበረታታ መሆኑም ተጠቅሷል።
በሐመረ ፍሬው
ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
