የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ፈተናውን ማለፍ የቻሉት 5 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ ናቸው – የትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 674 ሺህ 823 ተማሪዎች መካከል ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡት 36 ሺህ 409 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 5 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ ናቸው ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክተው ዛሬ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልጸዋል።

የዘንድሮው ዓመት አጠቃላይ ውጤት ካለፉት ሁለት ዓመታት አንጻር የተሻለ መሆኑንም ተናግረዋል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛው ውጤት የተመዘገበው ከትግራይ ክልል መሆኑን ያስታወቁት የትምህርት ሚኒስትር ብርሐኑ ነጋ (ፕ/ር) ውጤቱም ከ700ው 675 መሆኑን ጠቁመዋል፤ የቃላሚኖ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን አመላክተዋል።

ከ600ው በተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ 575 በአዲስ አበባ አክሲሊየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት መመዝገቡን አንስተዋል፡፡

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 1 ሺህ 220 የሚሆኑት ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም መካከል 384 ቱ ሴቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መግለጻቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *