፦በመዝገብ ቁጥር 333122 የዋለው ችሎት በይግባኝ ባዮች በእነ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ (4 ሰዎች) እና መልስ ሰጪ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (5 ሰዎች) ጉዳይ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ባዮች በዋናነት ያነሱት ነው።
- ግንቦት 5 2016 እና ሰኔ 4 2016 የተከናወኑ ህገወጥ የጠቅላላ ጉባኤ እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ እንዲታገድ
- የህዝብ እና የሀገር ሀብት እንዳይባክን ከደመወዝ ክፍያ ውጪ የባንክ አካውንት እንዲታገድ ጠይቀዋል
የይግባኝ መነሻቸውን ፍርድ ቤቱ የመረመረ ሲሆን አመልካቾችና ጠበቆች በሰጡት ምልሽ በዋናነት ህግና ስርዓት ተከብሮ ተቋሙን የመታደግ አላማና ወደነበረበት ከፍታ ለመመለስ ከመሻት የመነጨ ፍላጎት እና ቁጭት እንጂ የጥቅምም ሆነ የስልጣን ፍላጎት እንደሌላቸው ለፍርድ ቤት አስረድተዋል፡፡
ከስራ አስፈፃሚዎች ነውጠኝነትና ለስርዓትና ለህግ ያለመገዛት አዝማሚያ በስራ ማስኬጃ ሰበብ ብክነት እንዳይኖር እንዲሁም በሪፎርም በሚል ምክንያት የታቀዱ ብክነቶች ስለመኖራቸው መረጃ ስላለን ፍርድ ቤቱ አካውንቱን እንዲያግድ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ትእዛዝ ለባንኮችና ለዋና መስሪያ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
ሌላኛው ትእዛዝ ለኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በቀን 04/10/2016 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ የታገደ መሆኑን እንዲያውቁና እግዱን እንዲፈፅሙም ታዟል፡፡
የመልስ ሰጪዎችን ምላሽ ለመስማት ለመስከረም20 ፍርድቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም
