የአርሰናሉ አጥቂ ቡካዮ ሳካ መድፈኞቹ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን በማንሳት የ21 ዓመታት ጥበቃቸውን የሚቋጩት “በዚህ ዓመት ነው” አለ።
የሚኬል አርቴታ ቡድን ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ከማንቸስተር ሲቲ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።
አርሰናል በ2003-04 የውድድር ዘመን በአርሰን ቬንገር እየተመራ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ዋንጫ ካሸነፈ በኋላ ለፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ክብር አልበቃም።
እንግሊዛዊው ከሲቢኤስ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ “በራሳችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ማሳረፍ አልፈልግም። ሆኖም ዘንድሮ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንደምናሸንፍ አስባለሁ” ብሏል።
አቤል ጀቤሳ
መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም
