ከንቲባ አዳነች አቤቤ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት አበረከቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2016 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል።

በ2016 ትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ክፍለ ከተሞች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው።

ከንቲባዋ በመርሐ ግብሩ ለትምህርት ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤በቀጣይ የተሻለ ውጤት እንጠብቃለን ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *