በቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ከ10 ሚሊየን  በላይ ህዝብ  ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ፡፡

በቁልቢ በሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ  የንግስ በአል ፤ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ከ10 ሚሊየን  በላይ ታዳሚያን ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሜታ ወረዳ ቱሪዝም ቢሮ ለጣቢያችን አስታውቋል።

የቱሪዝም ቢሮው ሀላፊ ኡስኒያ ሸምሱ፤ባለፈው አመት ከ 7 ሚሊዮን በላይ የእምነቱ ተከታዮች እንደተገኙ አስታውሰዋል፡፡

ዘንድሮ በአከባቢዉ ያለዉ የሰላም ሁኔታ የተረጋጋ በመሆኑ የታዳሚያን ቁጥር ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልፀዋል፡፡

ሃላፊዋ ፤በዓሉን ለማክበር ወረዳው በቂ ዝግጅት አደርጎ ታዳሚያንን የመቀበል ስራ መጀመሩንም ነግረዉናል፡፡
 
ሆቴሎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት እንዲያቀርቡ ዝግጅት መደረጉንም ነው የተናገሩት።  

ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከሐረሪ ክልል፣ ከምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የደህንነት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ሃላፊዋ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *