“ከጦርነት ወደ አስተማማኝ ሰላም” በሚል ርዕስ 40ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ ተጀምሯል

የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ባዘጋጀው 40ኛው የጉሚ በለል መድረክ “ከጦርነት ወደ አስተማማኝ ሰላም” በሚል ርዕስ የተለያዩ አካላት በተገኙበት ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ውይይቱ በቅርቡ የመንግሥትንና የህዝብን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት በመፈረም እየገቡ ያሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላትን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላቱ መንግሥት “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” ብሎ ያቀረበውን ጥሪ በመቀበልና የሰላም አስፈላጊነትን በመረዳት መግባታቸው በክልሉ ሰላምን ከማጽናት ባሻገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳውም የጎላ መሆኑን የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

ከጦርነት ወደ አስተማማኝ ሰላም የሚደረገው ሽግግር የሚሳካው በውይይት እና በመግባባት መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የመንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተጠሪዎች እንዲሁም አባገዳዎች ተገኝተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *