በኢትዮጵያ ከ9 ሚሊየን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ዉጪ ናቸዉ ተባለ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ይፋ ያደረገዉ አንድ ሪፖርት በኢትዮጵያ በግጭት እና መፈናቀል ምክንያት ከ 9 ሚሊየን በላይ ህጻናት ከትምህርት ዉጪ መሆናቸዉን ያሳያል፡፡

በግጭት እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ከ 6ሺህ በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸዉንም ይፋ አድርጓል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት መርጃ ዩኒሴፍ ፤ 18 በመቶ የሚሆኑ የአገራችንን ተማሪዎች የሚይዙ ከ10 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች በግጭት እና በአየር ንብረት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡

በዚህ ምክንያትም ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥ የትምህርት ማዕከል የማግኘት ዕድላቸዉ ጠባብ ሆኗል ነዉ ያለዉ፡፡

ከትምህርት ገበታ ዉጪ የሆኑ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ልጆች ያሉባቸዉን ክልሎች ይፋ ያደረገዉ ሪፖርቱ፤ በአማራ 4.4 ሚሊየን ፣ በኦሮሚያ 3.2 ሚሊየን እና በትግራይ ክልል ደግሞ 1.2 ሚሊየን ተማሪዎች ከትምህርት ዉጪ መሆናቸዉን አስታዉቋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም በአማራ ክልል 4.7 ሚሊየን ልጆች ከትምህርት ገበታ ዉጪ መሆናቸዉን ገልጾ፤ በዚህ የትምህርት ዘመን 32 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ምዝገባ ማካሄዳቸዉን ማስታወቁ የሚታወስ ነዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

ታኀሣሥ 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *