ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግሪንላንድን እና የፓናማ ቦይን ለመያዝ ወታደራዊ ሃይል ከመጠቀም ወደኋላ አይሉም ተብሏል ።
ዶናልድ ትራምፕ ህዳር 5 ምርጫ ካሸነፈ በኋላ እሰራለሁ ወይንም አደርገዋለሁ ብለው ካስቀመጡት አጀንዳ አካል የሆነውን የፓናማ ካናልን እና የግሪንላንድን ጉዳይ ነው።
ይህን ተከትሎም ትራንፕ በማር-አ-ላጎ በትላንትናው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፓናማ እና ግሪንላንድን በተመለከተ ጋጠዘኞች ስላላቸው እቅድ ለአለም አረጋግጡ ብለው ላነሱት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ትራምፕ በምላሻቸው ፣ “አይ፣ በሁለቱም ላይ ላረጋግጥላቹ አልችልም ግን ይህን ማለት እችላለሁ፣ ለኢኮኖሚ ደህንነታች እንፈልገዋለን ብለዋል።
ምክንያቱም ደግሞ እነዚህ ሁለቱም ቦዮች ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ወሳኝ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ለመግባት እና ስራ ለመጀመር ሁለት ሳምንታት ቀርተውታል።
ቢሆንም ግን ለዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች እና የአሜሪካ አጋሮች ስጋቶች ብዙም ግምት ውስጥ ሳይገባ ጠበኛና ለሌሎችምቹ ያልሆ የውጭ ፖሊሲን ማውጣት ጀምሯል መባሉንም መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
በጃንዋሪ 20 ስልጣን የሚረከቡት ትራምፕ ካናዳን ወደ አሜሪካ የመቀየር እንዲሁም የሜክሲኮን ባህረ ሰላጤ ስም ወደ አሜሪካ ባህረ ሰላጤ ለመቀየር እየተንደረደሩ ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
ልኡል ወልዴ
ታኀሣሥ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
