ለዚህም የሞባይል ኔትዎርክ እና ኢንተርኔት ተጠቃሽ መሆናቸውን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ብቻ ወደ 22 ሺ ኪ/ሜ የሚጠጋ መስመር ሀገራችን ውስጥ እንዳለው ተነስቷል።
እንዲሁም በአሁን ሰአት 8 ሺ 5 መቶ የሞባይል ኔትዎርክ ማስተላለፊያ ታወር መዘርጋት መቻሉ ተጠቅሷል።
ሳፋሪኮም ደግሞ እስካሁን ወደ 3ሺ 5መቶ የሞባይል ኔትዎርክ ማስተላለፊያ ታዎሮችን ዘርግቶ በመላው ሀገሪቱ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተነግሯል ።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለሶስት ቀናት የሚይቆ የኢንተርኔት ልማት ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።
በጉባኤውም ኢንተርኔት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለማህበራዊ ትስስር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተነስቷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የኢጋድ ሀገራት የቴክኖሎጂ እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሮች ፣ከፍተኛ አመራሮች ፣የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ሐመረ ፍሬው
ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም
