በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ሊቨርፑል ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ኮዲ ጋክፖ ፣ መሐመድ ሳላህ ፣ ስቦዝላይ እና ቫን ዳይክ አስቆጥረዋል።
ሊቨርፑል ቶተንሀምን በድምር ውጤት 4ለ1 በማሸነፍ ለካራባኦ ካፕ ፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።
ሊቨርፑል ለካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ሲደርስ ይሄ ለ 15ተኛ ጊዜ ሲሆን በውድድሩም የዚን ያህል ጊዜ ለፍፃሜ የደርሰ ክለብ የለም።
ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ የፍፃሜው ጨዋታ መጋቢት 7/2017 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም
