በባለፉት አራት ወራት ዉስጥ አራት ህፃናት በታጣቂ ቡድኑ ታግተዉ መወሰዳቸዉንም ኢትዩ ኤፍም ሰምቷል።
መነሻዉን ከደብብ ሱዳን ያደረገዉ እና የኢትዮጵያ ድንበር በመጣስ ጥቃት እየፈፀመ የሚገኘዉ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂ ቡድን በክልሉ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ መቀጠሉን ሰምተናል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋምቤላ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ማበር ኮር በተለይም በክልሉ በሚገኙ የኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች ላይ የታጣቂ ቡድኑ በስፋት ጥቃት ስለመፈፀሙ ገልፀዋል።
ከአራት ወር በፊት ታጣቂ ቡድኑ ከአራት ህፃናት እገታ ዉጪ ሁለት የወርቅ አዉጪ ባለሀብት ግለሰቦች መግደሉን ሀላፊዉ ለጣቢያችን አስታዉቀዋል።
አሁንም የሙርሌ ታጣቂ ቡድን የጥቃት ሙከራዎች ቀድሞ ለመከላከል ክልሉ ስራዎች እንዳሉት ሀላፊዉ አንስተዋል።
የታገቱትን ህፃናት እና ከብቶችን በድርድር ለማስመለስ የደብብ ሱዳን መንግስት መረጋጋት አለመቻል የሚያስቸግር ሁኔታ ፈጥሯል ተብሏል።
ታጣቂ ቡድን በስፋት የበጋ ወቅት ላይ በክልሉ ዉስጥ የጥቃት እንቅስቃሴ እንደሚታይበት ተገልፆል።
የጋምቤላ ሰላም እና ፀጥታ ሀላፊዉ አቶ ማበር ኮር ይህንን ተከትሎ በቅርቡ ይህንን ለማስቆም ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ዉይይት ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸዉን ገልፀዋል።
የጋምቤላ ክልል አሁን ላይ ከሙርሌ እና ከኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የተወሰነ ጥቃት ዉጪ ክልሉ አንፃራዊ ሰላም እየታየበት መሆኑን ሀላፊዉ ተናግረዋል።
ቁምነገር አየለ
የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
