ኦክሎክ ቅሬታ ከነበረባቸው ማህበራት ከ16ቱ ማህበራት ጋር በእርቅ ለመፍታት ሲስማማ፤ 10 ማህበራት ግን አሁንም የህግ ጉዳዩን መርጠው በህግ ሂደት ላይ እንዳሉም ገልጿል።
የማህበራቱ ተወካዮች ፤ገንዘብ የሚፈልግ ገንዘብ መኪና ከሆነ መኪና እንዲሰጠን ከኦክሎክ ጋር ተስማምተናል ሲሉ ገልፀዋል።
የኦክሎክ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁን ፤ 1.2 ቢሊየን ብር ከህዝብ ቢሰበሰብም ለደንበኞቹ መኪና አላመጣም የሚለውን መረጃ የተሳሳተ እንደነበር እና 41 ሚሊየን ብር ብቻ እንደተሰበሰበ በማስረጃ ያሳየንበት መንገድ አለ ብለዋል፡፡
ምንም አይነት መኪና እየሰጡ አልነበረም የሚለው ክስ ልክ አለመሆኑን ለማሳየት ወደ 8 መቶ መኪናን በካሽ እና በብድር አስረክበናል ብለዋል።
ሀላፊው አክለውም የመኪናው ቁጥር ያንሳል የሚለው እውነት ቢሆንም ምንም አይነት መኪና አልሰጠም የሚለው ግን ልክ አይደለም ብለዋል።
ካሉት ማህበራት ውስጥ ወደ 220 ማህበራት ጉዳዩን ወደ ክስ መውሰዳቸውን ሰምተናል፡፡
አሁን ላይ ያሉትን ችግሮች በሽምግልና በእርቅ ለመፍታት ጥያቄ ካነሱት ከተወሰኑ ማህበራት ጋር ኦክሎክ መስማመቱ ተነግሯል፡፡ ከሌሎቹ የህግ ጉዳዩን ከመረጡት ጋር ደግሞ በህግ ሂደቱ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
የተቀሩን አስር ማህበራት አሁንም ሽምግልናን ምርጫቸው ካደረጉ በራችን ክፍት ነው ሲል ኦክሎክ ጨምሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
ለአለም አሰፋ
መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም
