በፈረንጆቹ 2024 የተበከሉ ከተሞች ተብለው በቀዳሚነት ከተቀመጡ 20 ከተሞች መካከል ከአንዱ በስተቀር ሁሉም እስያ ውስጥ እንደሚገኙ አዲስ የወጣ ጥናት አመልክቷል፡፡
ከእነዚህ ከተሞች መካከል13ቱ በአለማችን ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ባላት ሀገር ህንድ ውስጥ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡
ህንድ ካለፈው አመት ከነበራት ደረጃ ዝቅ ብትልም፤ አሁንም ከፍተኛ የአየር ብክለት ካለባቸው አገራት አንዷ ነች።
በዚህም ምክንያት አሁንም ከፍተኛ የጤና ጫና ያለው ሲሆን፤ የነዋሪዎቿን የዕድሜ ገደብ በ5.2 ዓመታት ቀንሶታል።
ሌሎች አራቱ ደግሞ በፓኪስታን አጎራባች ሀገር ፤ በቻይና እና በካዛክስታን በቅደም ተከተል ይገኛሉ።
ብቸኛዋ ከእስያ ውጪ የምትገኘው የቻድ ዋና ከተማ የሆነችው ኒጃሜና በመካከለኛው አፍሪካ የከፋ የአየር ብክለት ያለባት ሀገር የሚል ስያሜ እንደተሰጣት ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።
ሐመር ፍሬው
መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም
