በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአይደር ሆስፒታል የአስተዳደርና የልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ሀይለ ስላሴ፤ ሆስፒታሉ ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ባጋጠመዉ ችግር አሁን ላይ ከባድ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ከፕሪቶሪያል የሰላም ስምምነት በኋላም የተወሰነ የመድኃኒት ዕጥረት ነበረ ያሉት ዶ/ር ሀይለ ስላሴ ፤ ሆስፒታሉ የሚገባዉን በጀት እየተመደበለት ባለመሆኑ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል ነው ያሉት።
ሰራተኛው የ17 ወራት ደሞዝ እና የትርፍ ሰአት ክፍያ አልተከፈለውም ፤በዚህም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ብለዋል።
ካለው የትራንስፖርት መቆራረጥ በተጨማሪ ነዳጅ ለማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ ሰራተኞች በእግራቸዉ በመሄድ ህክምና እየሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተደጋጋሚ የመንግስት አካል ምላሽ እንዲሰጠን ጥያቄ ብናቀርብም እስካሁን ምንም ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም ብለዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
