ይህ የትራምፕ ንግግር ከተሰማው የሩስያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኩርስክ የተባለውን ግዛት እየጎበኙ መሆኑን ክሬምሊን ባስታወቀበት ጊዜ ነው።
የአሜሪካ ባለስልጣናት፤ በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ሊደረግ ስለሚችል የተኩስ አቁም ስምምነት ንግግር ለማድረግ ወደ ሞስኮ ማቅናታቸውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የትኛዎቹ የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ሞስኮ እንደተጓዙ አልገለጹም።
የቡድኑ ወደ ሩስያ የመጓዝ ዜና የተሰማው፤ በሳውዲ አረቢያ በተደረገው የአሜሪካ እና ዩክሬን ባለስልጣናት ስብሰባ ላይ የኪዬቭ ባለስልጣናት ለ30 ቀናት ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ከተነገረ በኋላ ነው።
ከዚህ ጉዞ አስቀድሞ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሮቢዮ “በእውነቱ ኳሱ እጃቸው ነው” ብለው ነበር። አሜሪካ፤ ይህንን ጦርነት ለመቋጨት ብቸኛው መንገድ የሰላም ስምምነት እንደሆነ እንደምታምንም ተናግረዋል።
የአሜሪካው ቡድን የተጓዘው፤ የሩስያውን ሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኩርስክ የተባለውን ግዛት እየጎበኙ መሆኑን ክሬምሊን ባስታወቀበት ጊዜ ነው።
ማክሰኞ ዕለት በጅዳ ከተደረገው ንግግር በኋላ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ስምምነት የተደረሰበትን “አዎንታዊ” እቅድ ሩስያ እንድትቀበለው የማድረግ ኃላፊነት አሜሪካ እንደሆነ ተናግረዋል።
ክሬምሊን በበኩሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እየተመለከተው መሆኑን የገለጸ ሲሆን በትራምፕ እና በፑቲን መካከል በስልክ ንግግር ሊደረግ እንደሚችልም ጠቁሟል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ የአየር ላንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲንን በቤተ መንግስታቸው በተቀበሉበት ወቅት፤ የተኩስ አቁሙን በተመለከተ “በጎ መልዕክት” መቀበላቸውን ገልጸዋል።
“በጎ መልዕክት ግን ምንም ነው” ያሉት ትራምፕ፤ “ይህ በጣም ከባድ ሁኔታ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
