“የኤርትራ መንግስት ለትግራይ ትርምስ ከሚሰሩ አካላት ውስጥ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ
የኤርትራ መንግስት ከፌድራል መንግስት ጋር ከፕሪቶሪያ ስምነት በኋላ እሰጣ ገባ ውስጥ ነው ለትግራይ ምስቅልቅልም እጃቸው ካሉባቸው አካላት አንዱ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ጌታቸው ትግራይ ውስጥ በሚፈጠረው ትርምስ እናተርፋለን በሚል የኤርትራ መንግስት እጁን አስገብቷል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው ያነሱት ነጥቦች ፦
በአሁኑ ሰዓት በብዙ የትግራይ አካባቢዎች የፌደራል መንግስት ሰራዊት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ወጥተዋል፡፡
የተለያዩ ጀነራሎች የፖለቲካ ጥቅም አገኛለው ብለው ከኤርትራ ጋር ንግግር የሚያደርጉ አሉ።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲቋቋም በፕሪቶሪያል ስምምነት መሰረት በፌደራል መንግስት እውቅና የተመሰረተ አስተዳዳደር ሆኖ ሳል ይህን አልቀበልም ያሉ የህግ ተቀባይነት ባላገኙ አንጃዎች የወረዳ እና የከተማ ማህተቦችን ቀምተው አስተዳዳሪ ነን ሲሉ የፌደራል መንግስት ዝም ይላል ብዬ አላስብም ሲሉ ተናግረዋል፡
ከአስር ሺ በላይ ታጣቂ ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ ይፈልግ ነበር በአንዳንድ ምክንያቶች ግን ትጥቅ ማስፈታቱ እንደቆመ ፡፡
የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሟላ መልኩ ከተፈጸመ ጊዜዓዊ አስተዳደሩ አያስፈለግም ምርጫ ማካሄድ ይቻላል፡፡
የፈናቃዮች ጉዳይም በፌደራል መንግስቱ እና በጊዜዓዊ አስተዳደሩ በቂ ትኩረት አልተሰጠውም ፖለቲካዊ ጨዋታው ለተፈናቃዮች አልሆነም ነበረ ይህም የችግሩ አካል ነው፡፡
ችግር ፈጣሪ ሽፍቶች ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ መጥተው ማህተም ቀምተናልና የመንግስትነት እውቅና ይሰጠን ቢሉ እንዳትገረሙም ብለዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
