ባለፉት 5 አመታት ውስጥ 1 መቶ 67 ሺህ ቤት ተገንብቶ ጥቅም ላይ አውለናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች ከ 17 ቢሊዮን ብር በላይ ውጭ ተደርጎ መንግስት ካሳ መከፈሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ አንስተዋል፡፡

አሁንም ከ 1መቶ ሺህ በላይ ቤቶች በመንግስት እና በግሉ ሴክተር እየተገነቡ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢህአዴግ ዘመን ከ1997 እሰከ 2010 ባለው 13 አመታት 160 ሺህ ገደማ ቤቶች ብቻ መገንባቱን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ባለፉት 5 አመታት ውሰጥ ግን ከ1 መቶ 67 ሺህ ቤት በላይ መገንባት እንደተቻለ አንስተዋል ፡፡

በሃገሪቱ ያለው የቤት ፍላጎት ሰፊ ቢሆንም ተጨማሪ ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ወደ ፊት ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ስራ መሰራቱን አስታውሰዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ህጋዊ ካርታ ኖሮት መሬት ወይም ካሳ ሳይከፈለው ለልማት የተነሳ አንድም ሰው እንደሌለም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

ለልማት ተነሺዎች ከ 17 ቢሊዮን ብር በላይ ውጭ ተደርጎ ካሳ መከፈሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ አንስተዋል፡፡

አቤል እስጤፋኖስ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *