ሩሲያ  በዩክሬን የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች   ላይ ሰፊ ጥቃት መጀመሯ ተሰምቷል

ሩሲያ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በዩክሬን የሃይል ማመንጫዎች ላይ ሰፊ የሆነ ጥቃት ከፍታለች።

በኬቭ እና ዛፖርዚያ ከተሞች በሚገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ አስራ ስምንት ፍንዳታዎች የተከሰቱ ሲሆን የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጡም ተዘግቧል፡፡

ምንም እንኳን ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን የሃይል ማመንጫዎችን እንደማያጠቁ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ስምምነት ላይ ቢደርሱም : የዩክሬን  ሩሲያ  የጋዝ ምርቷን ለአውሮፓ ገበያ የምታቀርብበትን እና  በክረስክ ግዛት በኩል የሚገኘው ቱቦ ላይ ጥቃት በመፈጸሟ ነው ጥቃቱ የተፈጸመው ተብሏል ዘገባው ፡፡

ከጥቂት ቀናት ወዲህ ሩሲያ በዩክሬን የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ መቀጠሏን የዘገበው ዘ ቴሌግራፍ ነው፡፡

ገነነ ብርሃኑ

መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *