የገንዘብ ሚኒስቴር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተግባራዊ የማድረግ ሃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የ8 ወራት የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
የፊሲካል ፖሊሲውን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት እና ለመሰረታዊ ግብዓቶች ከ300 ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ መደረጉን ሚኒትስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ አንስተዋል፡፡
በዚህም አጠቃላይ የመንግስትን ፋይናንስ በአግባቡ በማስተዳደር የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ፕሮግራም ውጤታማ በማድረግ ተቋሙ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በቀጣዩ 2018 በጀት ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ፕሮግራሙ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የዋጋ ንረቱ የሚጨምርበት ፍጥነት ይበልጥ እንዲቀንስ ጥረት እንደሚደረግ መጠቆሙንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሚያዚያ 01ቀን 2017 ዓ.ም
