ከመንግሥት የጤና ተቋማት የተሰረቁ መድሀኒቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በህገወጥ የመድሀኒት ዝዉዉር 1መቶ18 ሚሊየን ብር የሚገመቱ መድሀኒቶች ተገኝተዋል።

ከዚህም መካከል ከመንግሥት የጤና ተቋማት የተሰረቁ መድሀኒቶች ተገኝተዋል ተብሏል ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ዘዉዴ ባሳለፍነው ሳምንት በህገወጥ የመድሀኒት ዝዉዉር ላይ በተደረገ ቁጥጥር 118 ሚሊዮን ግምታዊ ዋጋ ያላቸዉን መድሀኒቶች መያዛቸዉን ገልፀዋል።

በአዳማ እና በአዲስ አበባ ከተሞች ላይ ባሉ 23 ቦታዎች ላይ በተደረገ የቁጥጥር ስራ እንደተያዘ ከኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ባለስልጣን ሰምተናል።

ከተያዙት መድሀኒቶች መካካል የወባ÷ የካንሰር ከመንግስት ተቋማት ተሰርቀዉ የወጡ የኘሮግራም መድሀኒቶች ይገኙበታል።

ከዚህ በተጨማሪ ግምታዊ ዋጋቸው 1መቶ50 ሚሊየን ብር የሆነ ጥቅም ላይ የማይውሉ የህክምና መሳሪያዎች ተይዘዋል ተብሏል።

በሳምንቱ ተደርጓል በተባለዉ የቁጥጥር ስራ በአጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸው ከ3መቶ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ህገወጥ ምርቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ከባለስልጣኑ ሰምተናል።

ከሕገወጥ ተግባሩ ጋር በተያያዘም 19 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ቁምነገር አየለ

ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *