አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ የትግል መንገዶችን እየዘጋ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመለከቱ።

ዓረና፣ ባይቶና እና የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በጋራ በሰጡት መግለጫ አዲሱ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሁሉንም ባገለለ መልኩ ካቢኔው አዋቅሯል ሲሉም ወቅሰዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ «የወታደራዊ አገዛዝ ባህርያት እየታየበት ነው» የሚሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በክልሉ በአንፃራዊነት በተሻለ ሁኔታ እየታየ ቆየ ያሉት አካታች ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን ለመቀየር እና ሁሉን ነገር በአንድ አካል ቁጥጥር ስር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ፓርቲዎቹ አክለውም አዲሱ ጊዜያዊ የክልሉ አስተዳደር በበርካቶች ተሳትፎ ተመስርቶ ከነበረው ምክር ቤት ጋር አብሮ ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆን፤ የዴሞክራሲ ግንባታ ተቋማትን ማፍረስ፤ እንዲሁም የተለየ አስተሳሰብ ያላቸውን አካላት እና የተቃውሞ ፓርቲ አባላትን ማሳደድ መኖሩንም ገልጸዋል ሲል ዶቼ ቬለ ዘግቧል።

ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *