በኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት 71 በመቶ ደርሷል ሲል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ገለፀ።

የተቀረው ህዝብ ንፅህናው ያልተጠበቀ ውሃ እንደሚጠቀምና ሃገሪቱ ንፅህናው የተጠበቀ ውሃን ለዜጎቿ ለማዳረስ በምታደርገው ጥረት፣ በተለይም በገጠራማው ክፍል መሰናክሎች እንዳሉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ይህ የተገለፀው አክሽን ፎር ዘ ኒዲ የተሰኘው ሃገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጄኔቫ ከሚገኘዉ አለም አቀፍ የውሃ፣ አካባቢ እና ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በውሃና በአካባቢ አያያዝ በጋራ ለመስራት ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በተስማሙበት መድረክ ነው::

በመድረኩ በህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ፤ ተያያዥ ሰብአዊ እና የልማት ድጋፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትም ተፈርሟል።

የመግባቢያ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማዳረስ በምታደርገው ጥረት መሰናክሎች እንዳሉ ገልፀው፣ በተለይም በገጠራማው አካባቢ ችግሩ እንደሚሰፋ ጠቅሰዋል።

መሰረታዊ የንፅህና አጠባበቅን በተመለከተም ከ10 በመቶ በታች ለሆነው የህብረተሰብ ክፍል ብቻ ተደራሽ እንደሚሆን በፈረንጆቹ 2020 የተደረገ ጥናት እንደሚያመላክት የተናገሩት ሚኒስቴር ዴኤታው፣ እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን በማቃልለ ረገድ አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወት ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል።

የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳሊሁ ሱልጣን ሂዉማን ብሪጅ ከአሁን ቀደም ለነጌሌ ሆስፒልና ለገጠራማ አካባቢዎች በ40 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለነጌሌ ሆስፒልና ለገጠራማ አካባቢዎች 80 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ተናግረዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት በታማኝነትና በቁርጠኝነት መስራት ይጠይቃል ተብሏል፡፡
አዲስ ዓለም አበበ

ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *