ወደ ሀገር የሚገቡና ከሀገር የሚወጡ እንስሳትና የእንስሳት ምርቶች ጥራት እንዲጠብቁ የሚያስችለዉ አዋጅ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 27ኛዉ መደበኛ ስብሰባ የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡

አዋጁ ወደ ሀገር የሚገቡና ከሀገር የሚወጡ እንስሳት እና የእንስሳት ምርቶች የዓለም የጤና ድርጅትን አሰራር እና ሕግ የተከተሉ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል።

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥርም ነው የተመላከተው፡፡

አዋጁ ሀገር ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንድታጎለብት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

ልኡል ወልዴ

ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *