በአዲስ አበባ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በጡት ካንሰር ህክምና ዙሪያ የስልጠና ንቅናቄ ሊሰጥ መሆኑ ተገለጻ ፡፡

ንቅናቄዉን የዘውዲቱ ጌታቸው ፋውንዴሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ‹‹ከተማ አቀፍ ንቅናቄ፤ የጡት ካንሰር ግንዛቤን ለማሳደግ›› በሚል መሪቃል ነዉ የተጀመረዉ፡፡

የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠናዉን የሚወስዱት በአሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ላይ ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎችን መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

ከተማ አቀፍ የጡት ካንሰር የአሠልጣኞች ግንዛቤን ማስጨበጫ ንቅናቄዉ በሦስት ዙር የሚካሄድ ነዉ ተባሏል፡፡

የመጀመሪያውን ዙር ከዛሬ ሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ፣ሁለተኛው ዙር ከግንቦት 14 እስከ 16 እንዲሁም ሦስተኛው ዙር ከግንቦት 21 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

የንቅናቄዉ ዓላማ የጤና ባለሙያዎች በቅድመ ምርመራ፣በሐኪምና ታካሚ መስተጋብር ስልቶች እንዲሁም በሪፈራል ዘዴዎች ላይ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን ለማሻሻል የሚያግዝ ነዉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የጡት ካንሰር ግንዛቤን ለማሻሻል፣ቅድመ ልየታን ለማበረታታትና ለጡት ካንሰር ታማሚዎች ጥራቱ የተረጋገጠ ህክምናን ተደራሽ ለማድረግ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *