ፖርቹጋል ከ ስፔን ጋር በመደበኛው ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቆ በመለያ ምት ፖርቹጋል 5ለ3 በማሸነፍ ነው የኔሽንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
የስፔንን ግብ ዙቢሜንዲ እና አኦያርዛባል ሲያስቆጥሩ ለፖርቹጋል ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሜንዴዝ ከመረብ አሳርፈዋል።
ፖርቹጋል ሁለተኛ የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫዋን ማሸነፍ ችላለች።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን 138ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።
ፖርቹጋል ስፔንን በ 21ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፋታለች።
ጋዲሳ መገርሳ
ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
