ፈረንሳይ በእስያ-ፓሲፊክ ክልል የኔቶ ጣልቃ ገብነትን እንደምትቃወም ቻይና ተስፋ አደርጋለሁ አለች

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን ኖኤል ባሮት ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ፈረንሳይ በእስያ ፓሲፊክ ክልል ውስጥ የኔቶ ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል።

ዋንግ ከ ውጭ ሚኒስትሩ ባሮት ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ በቤጂንግ የሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለፀው ፈረንሳይ ትክክለኛውን አቋም እንደምትይዝ እና የኔቶ በእስያ ፓሲፊክ ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ትቃወማለች የሚል ተስፋ አለው።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጋራ ነጻ ንግድን ለመጠበቅ እና የአንድ ወገን እና የጉልበተኝነት ድርጊቶችን መቃወም ያስፈልጋል ብለዋል።

ፈረንሳይ ቻይናን እንደ አጋር ትመለከታታለች እና ለቻይና ፖሊሲዎች አክብሮት እንዳላት የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን ኖኤል ባሮት ከቻይና አቻቸው ዋንግ ዪን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ላይ ገልፀዋል።

ሁለቱም ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል የህዝብ ለህዝብ እና ለባህል ልውውጥ አጽንኦት እንደሚሰጡ ገልፀዋል።

ባሮት እና ዋንግ እንደ ዩክሬን ፍልስጤም እና እስራኤል እንዲሁም የኢራን የኒውክሌር ጉዳይ ባሉ አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ሲል አናዱሉ ዘግቧል።

ገነነ ብርሃኑ

ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *