ይህ የተባለዉ በትናንትናው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባካሄደው በ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ባለድርሻ አካላት ፎረም ላይ ነዉ።
በዚህም 2013 አ.ም በፌደራሉ ዋና ኦዲተር የፋይናንስ ጉድለት የተኘባቸዉ የመንግስት ተቋማት ከተገኘባቸዉ ጉድለት ዉስጥ 0.63 በመቶ ብቻ ተመላሽ ሲደረግ ነበር ተብሏል።
አንድ የቋሚ ኮሚቴ አባል በመድረኩ እንደገለፁት ይህ ማለት ለ2018 አመት የተያዘውን በጀት መሰረት አድርገን ስናየዉ የሁለት ክልሎች በጀት መሸፈን የሚችል ብር እንዳልተመለሰ ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።
የፌደራሉ ምክትል ዋና ኦዲተር አቶ አበራ ታደሰ ከተቋማቱ 0.63 በመቶ ተመላሽ ሲደረግ እንደነበር አስታዉሰዉ ሆኖም በ2016 አመት ወደ 14 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል።
ሆኖም ቀሪ ስራዎች አሉ ያሉት አቶ አበራ ነገር ግን መመዘኛዉ የገንዘብ መመለስ ብቻ ሳይሆን ኦዲት ብዙ ማሻሻያዎችን የሚሰጥ በመሆኑ ተሻሽሏል ብለን እያቀረብን ያለነዉ ብለዋል።
የፍትህ ሚኒስትሯ ሃና አርአያስላሴ በበኩላቸዉ በ2015 በጀት ዓመት ኦዲት ግኝቶችን መሰረት በማድረግ ከዋና ኦዲተር በደረሱ 28 ተቋማት ላይ ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ገልፀዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር የሺእመቤት ተስፋዬ ከኦዲት ግኝት ጋር በተያያዘ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ የተጀመረባቸዉ 5 የመንግስት ተቋማት መኖራቸዉን ገልፀዋል።
ከነዚህም ዉስጥ የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት እና ወሎ ተርሸሪ ኬር ህክምና እና ማስተማሪያ እንዲሁም ሁለት ዩንቨርስቲዎች ይገኙበታል።
ከዚያ በተጨማሪም በ2017 አ.ም ከኦዲት ግኝት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ ምርመራ እንዲካሄድባቸዉ በተሰጠ አቅጣጫ አስር ተቋማት ላይ ጥናት መደረጉን የፌደራሉ ፀረሙስና ኮምሽን ተናግሯል።
ቁምነገር አየለ
ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም
